22 የከነዓን አባት፣ ካም የአባቱን ዕርቃነ ሥጋ አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው።
23 ሴምና ያፌት ግን ልብስ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉና የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው የኋሊት በመሄድ የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ ሸፈኑ።
24 ኖኅ ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ፣ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን ዐወቀ፤
25 እንዲህም አለ፤“ከነዓን የተረገመ ይሁን፤ለወንድሞቹም፣ የባሪያ ባሪያ ይሁን።”
26 ደግሞም፤“የሴም አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ይባረክ፤ከነዓንም የሴም ባሪያ ይሁን።”
27 “እግዚአብሔር (ኤሎሂም) የያፌትን ግዛት ያስፋ፤ያፌት በሴም ድንኳኖች ይኑር፤ከነዓንም የእርሱ ባሪያ ይሁን” አለ።
28 ኖኅ ከጥፋት ውሃ በኋላ 350 ዓመት ኖረ፤