19 ነገር ግን የዚህ ዓለም ውጣ ውረድ፣ የሀብት አጓጊነት እንዲሁም የሌሎች ነገሮች ምኞት ቃሉን አንቀው በመያዝ ፍሬ እንዳ ያፈራ ያደርጉታል።
20 ሌሎቹ በመልካም መሬት ላይ የተዘራውን ዘር ይመስላሉ፤ እነዚህም ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉና ሠላሳ፣ ሥልሳ፣ መቶም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።”
21 እንዲህም አላቸው፤ “መብራት አምጥታችሁ ከዕንቅብ ወይም ከዐልጋ ሥር ታስቀምጣላችሁን? የምታስቀምጡት በመቅረዙ ላይ አይደለምን?
22 ስለዚህ ተደብቆ የማይገለጥ፣ ተሸሽጎ ወደ ብርሃን የማይወጣ የለም፤
23 ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ።”
24 በመቀጠልም፣ “ስለምትሰሙት ነገር ጥንቃቄ አድርጉ፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል፤ እንዲያውም ከዚያ የበለጠ ይጨመርላችኋል።
25 ላለው ይጨመርለታል፤ ከሌለው ላይ ግን፣ ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል” አላቸው።