3 ሁለተኛው መልአክ ጽዋውን በባሕር ላይ አፈሰሰ፤ ባሕሩም እንደ ሞተ ሰው ደም ሆነ፤ በባሕሩ ውስጥ የሚኖሩ ሕይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ ሞቱ።
4 ሦስተኛው መልአክ ጽዋውን በወንዞችና በውሃ ምንጮች ላይ አፈሰሰ፤ እነርሱም ደም ሆኑ።
5 ከዚያም በውሆች ላይ ሥልጣን ያለው መልአክ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤“ያለህና የነበርህ ቅዱሱ ሆይ፤እንዲህ ስለ ፈረድህ፣አንተ ጻድቅ ነህ፤
6 የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ፣አንተም ደግሞ ደም እንዲጠጡ አደረግሃቸው፤ ይህ የሚገባቸው ነውና።”
7 እንዲሁም ከመሠዊያው እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፤“አዎን፤ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ ሆይ፤ፍርድህ እውነትና ጽድቅ ነው።”
8 አራተኛውም መልአክ ጽዋውን በፀሓይ ላይ አፈሰሰ፤ ፀሓይም ሰዎችን በእሳት እንድታቃጥል ኀይል ተሰጣት።
9 እነርሱም በታላቅ ሐሩር ተቃጠሉ፤ በእነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ እንጂ ንስሓ አልገቡም፤ ክብርም አልሰጡትም።