ራእይ 18:17-23 NASV

17 ያ ሁሉ ሀብት በአንድ ሰዓት ውስጥ ጠፋ።”“የመርከብ አዛዦች ሁሉ፣ በመርከብ የሚጓዙ መንገደኞች ሁሉ፣ የመርከብ ሠራተኞችና ኑሮአቸውን በባሕር ላይ የመሠረቱ ሁሉ በሩቅ ይቆማሉ።

18 እርሷ ስትቃጠል የሚወጣውን ጢስ ሲያዩ፣ ‘እንደዚች ያለ ታላቅ ከተማ ከቶ የት አለ?’ እያሉ ይጮኻሉ።

19 በራሳቸውም ላይ አቧራ ነስንሰው እያለ ቀሱና እያዘኑ እንዲህ ብለው ጮኹ፤“ ‘በባሕር ላይ መርከቦች ያላቸው ሁሉ፣በእርሷም ሀብት የበለጸጉ፣ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት!በአንድ ሰዓት ውስጥ ጠፍታለች።

20 ሰማይ ሆይ፤ በእርሷ ላይ ሐሤትአድርግ፤ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያትም ሐሤት አድርጉ፤በእናንተ ላይ ባደረሰችው ነገርእግዚአብሔር ፈርዶባታልና።’ ”

21 ከዚያም አንድ ብርቱ መልአክ፣ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚመስል ድንጋይ አንሥቶ ወደ ባሕር ወረወረው፤ እንዲህም አለ፤“ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን፣እንዲህ ባለ ኀይል ትወረወራለች፤ተመልሳም አትገኝም።

22 የበገና ደርዳሪዎችና የሙዚቀኞች ድምፅ፣የዋሽንትና የመለከት ነፊዎች ድምፅ፣ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይሰማም፤የእጅ ጥበብ ባለ ሙያ፣ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይገኝም፤የወፍጮ ድምፅም፣ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይሰማም።

23 የመብራት ብርሃን፣ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይበራም፤የሙሽራውና የሙሽራዪቱ ድምፅ፣ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይሰማም፤ነጋዴዎችሽ የዓለም ታላላቅ ሰዎች ነበሩ፤በአስማትሽም ሕዝቦች ሁሉ ስተዋል።