ራእይ 18:4-10 NASV

4 ከዚያም ከሰማይ ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤“ሕዝቤ ሆይ፤ በኀጢአቷ እንዳትተባበሩ፣ከመቅሠፍቷም እንዳትካፈሉ፣ከእርሷ ውጡ፤

5 ኀጢአቷ እስከ ሰማይ ድረስ ተከምሮአልና፤እግዚአብሔርም ዐመፃዋን አስታውሶአል።

6 በሰጠችው መጠን ብድራቷን መልሱላት፤ለሠራችው ሁሉ ዕጥፍ ክፈሏት፤በቀላቀለችውም ጽዋ ዕጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት።

7 ለራሷ ክብርና ምቾት የሰጠችውን ያህል፣ሥቃይና ሐዘን ስጧት፤በልቧም እንዲህ እያለች ትመካለች፤“እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤መበለትም አይደለሁም፤ ከቶምአላዝንም፤”

8 ስለዚህ መቅሠፍቶቿ በአንድ ቀን ይመጡባታል፤ሞት፣ ሐዘንና ራብ ይሆኑባታል፤የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ስለ ሆነ፣በእሳት ትቃጠላለች።

9 “ከእርሷ ጋር ያመነዘሩና በምቾት የኖሩ የምድር ነገሥታት፣ እርሷ ስትቃጠል የሚወጣውን ጢስ ሲያዩ ስለ እርሷ ያለቅሳሉ፤ ያዝናሉም።

10 ሥቃይዋንም በመፍራት በሩቅ ቆመው እንዲህ ይላሉ፤“አንቺ ታላቂቱ ከተማ ወዮልሽ! ወዮልሽ!”አንቺ ባቢሎን ብርቱዪቱ ከተማ፣ፍርድሽ በአንድ ሰዓት ውስጥ መጥቶአል።”