1 “ከዚህ በኋላ የብዙ ሰዎችን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ሃሌ ሉያ!ማዳን፣ ክብርና ኀይል የአምላካችን ነው፤
2 ፍርዱ እውነትና ጽድቅ ነውና፤በዝሙቷ ምድርን ያረከሰችውን፣ታላቂቱን አመንዝራ ፈርዶባታል፤ስለ አገልጋዮቹም ደም ተበቅሏታል።”
3 ደግሞም እንዲህ አሉ፤“ሃሌ ሉያ!ጢስ ከእርሷ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል።”
4 ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጡራን በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው አምላክ ወድቀው ሰገዱ፤ እንዲህም አሉ፤“አሜን፣ ሃሌ ሉያ!”
5 ከዚህ በኋላ እንዲህ የሚል ድምፅ ከዙፋኑ ወጣ፤“እናንተ አገልጋዮቹ ሁሉ፣እርሱን የምትፈሩ፣ታናናሾችና ታላላቆችም፣አምላካችንን አመስግኑ!”
6 ደግሞም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ኀይለኛ ወራጅ ውሃ ድምፅ፣ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ የሚመስል እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ሃሌ ሉያ!ሁሉን ቻይ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።
7 የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ፣የእርሱም ሙሽራ ራሷን ስላዘጋጀች፣ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግክብርም እንስጠው።