12 እንዲህም ይሉ ነበር፤“አሜን፤ውዳሴና ክብር፣ጥበብ፣ ምስጋናና፣ ሞገስ፣ኀይልና ብርታትም፣ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን፤አሜን።”
13 ከዚያም ከሽማግሌዎቹ አንዱ፣ “እነዚህ ነጭ ልብስ የለበሱት እነማን ናቸው? ከወዴትስ መጡ?” አለኝ።
14 እኔም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ታውቃለህ” አልሁት።እርሱም እንዲህ አለኝ፤ እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው “አንጽተዋል።
15 ስለዚህ፣“በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ሆነው፣ቀንና ሌሊት በመቅደሱ ያገለግሉታል፤በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው ድንኳኑንበላያቸው ይዘረጋል፤
16 ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፤ከዚህም በኋላ አይጠሙም፤ፀሓይ አይመታቸውም፤ሐሩሩም ሁሉ አያቃጥላቸውም፤
17 ምክንያቱም በዙፋኑ መካከል ያለውበግ እረኛቸው ይሆናል፤ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭም ይመራቸዋል፤እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”