ዕብራውያን 4:2-8 NASV

2 ለእነዚያ እንደ ተሰበከ ለእኛም ደግሞ የምሥራቹ ቃል ተሰብኮልናልና። ነገር ግን ሰሚዎቹ ቃሉን ከእምነት ጋር ስላላዋሐዱት አልጠቀማቸውም።

3 እኛ ያመንነው ግን ወደዚያ ዕረፍት እንገባለን፤ እግዚአብሔርም፣“ስለዚህ በቍጣዬ እንዲህ ብዬ ማልሁ፤‘ወደ ዕረፍቴ ከቶ አይገቡም’ ” ብሎአል።ይሁን እንጂ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የእርሱ ሥራ ተከናውኖአል።

4 ስለ ሰባተኛውም ቀን በአንድ ስፍራ፣ “በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ዐረፈ” ብሎአልና።

5 ቀደም ባለው ክፍል ደግሞ፣“ወደ ዕረፍቴ ከቶ አይገቡም” ይላል።

6 ወደ ዕረፍቱ ገና የሚገቡ አንዳንዶች አሉ፤ ቀድሞ የምሥራቹ ቃል የተሰበከላቸው ባለመታዘዛቸው ምክንያት ወደ ዕረፍት አልገቡም።

7 ስለዚህ እግዚአብሔር፣ “ዛሬ” ብሎ እንደ ገና አንድን ቀን ወሰነ፤ ይህም ከብዙ ዘመን በኋላ በዳዊት በኩል፣“ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣ልባችሁን አታደንድኑ”ተብሎ ቀደም ሲል እንደ ተነገረው ነው።

8 ኢያሱ ዕረፍትን ሰጥቶአቸው ቢሆን ኖሮ፣ ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ሌላ ቀን ባል ተናገረ ነበር።