15 ከዚያም በልቤ፣“የሞኙ ዕድል ፈንታ በእኔም ላይ ይደርሳል፤ታዲያ ጠቢብ በመሆኔ ትርፌ ምንድን ነው?” አልሁ።በልቤም፣“ይህም ደግሞ ከንቱ ነው” አልሁ።
16 ጠቢቡም ሰው እንደ ሞኙ ለዘላለም አይታወስምና፤በሚመጡት ዘመናት ሁለቱም ይረሳሉ።ለካ፣ ጠቢቡምእንደ ሞኙ መሞቱ አይቀርም!
17 ስለዚህ ከፀሓይ በታች የሚሠራው ሥራ አሳዛኝ ስለ ሆነብኝ ሕይወትን ጠላሁ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
18 ከፀሓይ በታች የደከምሁበትን ነገር ሁሉ ጠላሁት፣ ከኋላዬ ለሚመጣው የግድ እተውለታለሁና።
19 እርሱ ጠቢብ ወይም ሞኝ ይሆን እንደሆነ ማን ያውቃል? ሆኖም ከፀሓይ በታች ድካሜንና ችሎታዬን ባፈሰ ስሁበት ሥራ ሁሉ ላይ ባለቤት ይሆንበታል፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።
20 ስለዚህ ከፀሓይ በታች በደከምሁበት ነገር ሁሉ ላይ ልቤ ተስፋ መቊረጥ ጀመረ፤
21 ምክንያቱም ሰው ሥራውን በጥበብ፣ በዕውቀትና በብልኀት ሠርቶ፣ ከዚያ ያለውን ሁሉ ለሌላ ላልለፋበት ሰው ይተውለታል። ይህም ደግሞ ከንቱና ትልቅ ጒዳት ነው።