1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የሞዓብ ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤የኤዶምን ንጉሥ ዐጥንት፣ዐመድ እስኪሆን ድረስ አቃጥሎአልና፤
2 የቂርዮትን ምሽጎች እንዲበላ፣በሞዓብ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤ሞዓብ በጦርነት ጩኸትና በመለከት ድምፅ መሐል፣በታላቅ ሁካታ ውስጥ ይሞታል።
3 ገዧን እደመስሳለሁ፣አለቆቿንም ሁሉ ከንጉሥዋ ጋር እገድላለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር።
4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣ይልቁን ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤አባቶቻቸው በተከተሏቸው አማልክት፣በሐሰት አማልክት በመመራት ስተዋልና።
5 የኢየሩሳሌምን ምሽጎች እንዲበላ፣በይሁዳ ላይ እሳት እሰዳለሁ።
6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የእስራኤል ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ጻድቁን ስለ ጥሬ ብር፣ችግረኛውንም ስለ ጥንድ ጫማ ይሸጡታልና።