7 የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤አባትህን ጠይቅ፤ ይነግርሃልም፤ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ያስረዱሃል።
8 ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ፣የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፣በእስራኤል ልጆች ቊጥር ልክ፣የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ፤
9 የእግዚአብሔር (ያህዌ) ድርሻ የገዛ ሕዝቡ፣ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና።
10 እርሱን በምድረ በዳ፣ባዶና ጭው ባለ በረሓ ውስጥ አገኘው፤ጋሻ ሆነው፤ ተጠነቀቀለትም፤እንደ ዐይኑ ብሌን ጠበቀው።
11 ንስር ጎጆዋን በትና፣በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፣እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ፣በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፣
12 እግዚአብሔር (ያህዌ) ብቻ መራው፤ምንም ባዕድ አምላክ አብሮት አልነበረም።
13 በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፤የዕርሻንም ፍሬ መገበው፤ከዐለት ድንጋይ ማር አበላው፤ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው።