2 “እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ተሰብሰቡና ስሙ፤አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ፤
3 “ሮቤል፣ አንተ የበኵር ልጄ ነህ፤ኀይሌና የጒብዝናዬም መጀመሪያ፤በክብር ትልቃለህ በኀይልምትበልጣለህ።
4 እንደ ውሃ የዋለልህ ነህና እልቅናአይኖርህም፤የአባትህን መኝታ ደፍረሃል፤ምንጣፌንም አርክሰሃል።
5 ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች፣ሰይፎቻቸው የዐመፅ መሣሪያዎች ናቸው።
6 ወደ ሸንጎአቸው አልግባ፤ጉባኤያቸው ውስጥ አልገኝ፤በቍጣ ተነሣሥተው ሰዎችን ገድለዋል፤የበሬዎችንም ቋንጃ እንዳሻቸው ቈራርጠዋል።
7 እጅግ አስፈሪ የሆነ ቍጣቸው፣ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፤በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ።
8 “ይሁዳ፣ ወንድሞችህ ይወድሱሃል፤እጅህም የጠላቶችህን ዐንገት ዐንቆ ይይዛል፤የአባትህ ልጆች በፊትህ ተደፍተው ይሰግዱልሃል።