17 “እግዚአብሔር ሆይ፤ የአሦር ነገሥታት እነዚህን አሕዛብንና ምድራቸውን በርግጥ አጥፍተዋል።
18 አማልክቶቻቸውን በእሳት ውስጥ ጥለው አቃጥለዋቸዋል፤ በሰው እጅ የተሠሩ ዕንጨትና ደንጊያ ብቻ እንጂ አማልክት አልነበሩምና።
19 አሁንም እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ የምድር መንግሥታት ሁሉ እግዚአብሔር አንተ ብቻ አምላክ መሆንህን እንዲያውቁ፣ ከእጁ አድነን።”
20 ከዚያም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘በአሦር ንጉሥ በሰናክሬም ላይ ወደ እኔ ያቀረብኸውን ልመና ሰምቻለሁ።
21 እንግዲህ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤“ ‘ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ፣ትንቅሃለች፤ ታቃልልሃለችም፤የኢየሩሳሌም ልጅ፣አንተ በላይዋ ስትበር ራሷን ትነቀንቅብሃለች።
22 ለመሆኑ የሰደብኸውና ያቃለልኸው ማንን ነው?ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው?ዐይንህንስ በኵራት ያነሣኸው በማን ላይ ነው?በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው እንዴ?
23 በመልእክተኞችህ አማካይነት፣በአምላክ ላይ የስድብ መዓት አውርደሃል፤እንዲህም ብለሃል፤“በብዙ ሠረገሎቼ፣የተራሮቹን ከፍታ፣የሊባኖስንም የመጨረሻ ጫፍ ወጥቻለሁ፤ረጃጅም ዝግባዎቹን፣ምርጥ የሆኑ ጥዶቹንም ቈርጫለሁ፤ወደ ሩቅ ዳርቻዎቹ፣ወደ ውብ ደኖቹም ደርሻለሁ።”