2 ነገሥት 19:21-27 NASV

21 እንግዲህ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤“ ‘ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ፣ትንቅሃለች፤ ታቃልልሃለችም፤የኢየሩሳሌም ልጅ፣አንተ በላይዋ ስትበር ራሷን ትነቀንቅብሃለች።

22 ለመሆኑ የሰደብኸውና ያቃለልኸው ማንን ነው?ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው?ዐይንህንስ በኵራት ያነሣኸው በማን ላይ ነው?በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው እንዴ?

23 በመልእክተኞችህ አማካይነት፣በአምላክ ላይ የስድብ መዓት አውርደሃል፤እንዲህም ብለሃል፤“በብዙ ሠረገሎቼ፣የተራሮቹን ከፍታ፣የሊባኖስንም የመጨረሻ ጫፍ ወጥቻለሁ፤ረጃጅም ዝግባዎቹን፣ምርጥ የሆኑ ጥዶቹንም ቈርጫለሁ፤ወደ ሩቅ ዳርቻዎቹ፣ወደ ውብ ደኖቹም ደርሻለሁ።”

24 “በሌሎች አገሮችም የውሃ ጒድጓዶች ቈፍሬአለሁ፤በዚያም ውሃ ጠጥቻለሁ፤በእግሬ ጫማዎችም፣የግብፅን ምንጮች ሁሉ ረግጬ አድርቄአለሁ።”

25 “ ‘ከብዙ ጊዜ በፊት፣ይህን እኔ እንዳደረግሁት አልሰማህም ነበርን?ዕቅዱን ገና ድሮ አውጥቼ፣አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ይህም የተመሸጉትን ከተሞች፣አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።

26 የሚኖሩባቸውም ሰዎች ኀይላቸው ተሟጦ አልቆአል፤ደንግጠውም የኀፍረት ማቅ ለብሰዋል፤ሜዳ ላይ እንደ በቀለ ተክል፣ገና እንዳልጠነከረ የቡቃያ ሥር፣በቤት ጣራ ላይ በቅሎ፣ገና ሳያድግ እንደ ጠወለገ ሣርም ሆነዋል።

27 “ ‘የት እንደምትቀመጥ፣መቼ መጥተህ መቼ እንደምትሄድ፣በእኔም ላይ የተቈጣኸውን ቊጣ ዐውቃለሁ።