23 በመልእክተኞችህ አማካይነት፣በአምላክ ላይ የስድብ መዓት አውርደሃል፤እንዲህም ብለሃል፤“በብዙ ሠረገሎቼ፣የተራሮቹን ከፍታ፣የሊባኖስንም የመጨረሻ ጫፍ ወጥቻለሁ፤ረጃጅም ዝግባዎቹን፣ምርጥ የሆኑ ጥዶቹንም ቈርጫለሁ፤ወደ ሩቅ ዳርቻዎቹ፣ወደ ውብ ደኖቹም ደርሻለሁ።”
24 “በሌሎች አገሮችም የውሃ ጒድጓዶች ቈፍሬአለሁ፤በዚያም ውሃ ጠጥቻለሁ፤በእግሬ ጫማዎችም፣የግብፅን ምንጮች ሁሉ ረግጬ አድርቄአለሁ።”
25 “ ‘ከብዙ ጊዜ በፊት፣ይህን እኔ እንዳደረግሁት አልሰማህም ነበርን?ዕቅዱን ገና ድሮ አውጥቼ፣አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ይህም የተመሸጉትን ከተሞች፣አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው።
26 የሚኖሩባቸውም ሰዎች ኀይላቸው ተሟጦ አልቆአል፤ደንግጠውም የኀፍረት ማቅ ለብሰዋል፤ሜዳ ላይ እንደ በቀለ ተክል፣ገና እንዳልጠነከረ የቡቃያ ሥር፣በቤት ጣራ ላይ በቅሎ፣ገና ሳያድግ እንደ ጠወለገ ሣርም ሆነዋል።
27 “ ‘የት እንደምትቀመጥ፣መቼ መጥተህ መቼ እንደምትሄድ፣በእኔም ላይ የተቈጣኸውን ቊጣ ዐውቃለሁ።
28 በእኔ ላይ በመቈጣትህ፣ንቀትህም ወደ ጆሮዬ ስለ ደረሰ፣ስናጋዬን በአፍንጫህ አደርጋለሁ፤ልጓሜን በአፍህ አገባለሁ፤በመጣህበትም መንገድእንድትመለስ አደርጋለሁ።’
29 “ሕዝቅያስ ሆይ፤ ምልክቱ ይህ ነው፤“በዚህ ዓመት በገዛ እጁ የበቀለውን፣በሚመጣው ዓመት ደግሞ የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤በሦስተኛው ዓመት ግን ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁ፤ወይንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።