27 “ ‘የት እንደምትቀመጥ፣መቼ መጥተህ መቼ እንደምትሄድ፣በእኔም ላይ የተቈጣኸውን ቊጣ ዐውቃለሁ።
28 በእኔ ላይ በመቈጣትህ፣ንቀትህም ወደ ጆሮዬ ስለ ደረሰ፣ስናጋዬን በአፍንጫህ አደርጋለሁ፤ልጓሜን በአፍህ አገባለሁ፤በመጣህበትም መንገድእንድትመለስ አደርጋለሁ።’
29 “ሕዝቅያስ ሆይ፤ ምልክቱ ይህ ነው፤“በዚህ ዓመት በገዛ እጁ የበቀለውን፣በሚመጣው ዓመት ደግሞ የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤በሦስተኛው ዓመት ግን ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁ፤ወይንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።
30 አሁንም ከዳዊት ቤት የተረፉት፣ሥራቸውን ወደ ታች ይሰዳሉ፤ ወደ ላይም ፍሬ ያፈራሉ።
31 ከኢየሩሳሌም በሕይወት የተረፉት፣ከጽዮን ተራራም ከሞት ያመለጡት ይወጣሉና። የእግዚአብሔር ቅናት ይህን ታደርጋለች።
32 “እንግዲህ እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፤“ወደዚች ከተማ ፈጽሞ አይገባም፤አንዲትም ፍላጻ አይወረውርባትም፤ጋሻ አንግቦ ወደ እርሷ አይቀርብም፤በዐፈርም ቊልል አይከባትም።
33 በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይሄዳል፤ተመልሶ ይሄዳታል እንጂ ወደዚች ከተማ ፈጽሞ አይገባም፤ይላል እግዚአብሔር።