2 ነገሥት 3:8-14 NASV

8 ኢዮሣፍጥም፣ “የምንዘምተው በየትኛው መንገድ ነው” ብሎ ጠየቀው፤ኢዮራምም “በኤዶም ምድረ በዳ አልፈን ነው” ሲል መለሰለት።

9 ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ከይሁዳ ንጉሥና ከኤዶም ንጉሥ ጋር ለመዝመት ተነሣ። ሰባት ቀን ከዞሩም በኋላ ለሰራዊቱም ሆነ ለእንስሶቻቸው የተረፈ ውሃ አልነበረም።

10 የእስራኤልም ንጉሥ፣ “ወዮ! እግዚአብሔር እኛን ሦስት ነገሥታት የጠራን ለሞዓብ አሳልፎ ሊሰጠን ነውን?” አለ።

11 ኢዮሣፍጥ ግን፣ “በእርሱ አማካይነት እግዚአብሔርን ለመጠየቅ እንድንችል፣ የእግዚአብሔር ነቢይ እዚህ የለምን?” በማለት ጠየቀ።ከእስራኤል ንጉሥ የጦር አለቆችም አንዱ፣ “ቀድሞ የኤልያስን እጅ ያስታጥብ የነበረው፤ የሣፋጥ ልጅ ኤልሳዕ በዚህ አለ” ብሎ መለሰለት።

12 ኢዮሣፍጥም፣ “የእግዚአብሔር ቃል ከእርሱ ዘንድ ይገኛል” አለ፤ ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ፣ ኢዮሣፍጥና የኤዶም ንጉሥ አብረው ወደ እርሱ ወረዱ።

13 ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ፤ “ከአንተ ጋር ምን የሚያገናኘን ጒዳይ አለና መጣህ፤ አሁን የአባትህና የእናትህ ነቢያት ወዳሉበት ሂድ” አለው።የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ፣ “ይህማ አይሆንም፤ በሞዓብ እጅ አሳልፎ ሊሰጠን እኛን ሦስት ነገሥታት አንድ ላይ የጠራን እግዚአብሔር ነው” አለ።

14 ኤልሳዕም እንዲህ አለው፤ “የማገለግለው ሕያው እግዚአብሔርን፣ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ባላከብር ኖሮ፣ አንተን አላይም ወይም ጒዳዬ አልልህም ነበር።