13 ኤልሳዕም፣ “ ‘ለእኛ ስትይ በጣም ተቸግረሻል፣ ምን እንዲደረግልሽ ትፈልጊአለሽ? ለንጉሡ ወይስ ለሰራዊቱ አዛዥ የምንነግርልሽ ጒዳይ አለን?’ ብለህ ጠይቃት” አለው።ሴቲቱም መልሳ፣ “እኔ እኮ የምኖረው በገዛ ወገኖቼ መካከል ነው” አለችው።
14 ኤልሳዕም፣ “ታዲያ ምን ይደረግላት” ሲል ጠየቀ።ግያዝም፣ “ልጅ እኮ የላትም፤ ባሏም ሸምግሎአል” አለ።
15 ኤልሳዕም፣ “በል እንግዲያው ጥራት” አለው፤ እርሱም ጠርቶአት መጥታ እበራፉ ላይ ቆመች።
16 ኤልሳዕም የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ” አላት፤እርሷም፣ “አይደለም ጌታዬ፣ አንተ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ ኋላ አገልጋይህን መዋሸት እንዳይሆንብህ!” አለችው።
17 ሴትዮዋም ፀነሰች፤ ኤልሳዕ እንደ ነገራትም በተባለው ጊዜ ወንድ ልጅ ወለደች።
18 ሕፃኑ አደገ፤ አንድ ቀንም አባቱ ከዐጫጆች ጋር ወደነበረበት ቦታ ሄደ።
19 አባቱንም፣ “ራሴን! ራሴን!” አለው። አባቱም አገልጋዩን፣ “ተሸክመህ ወደ እናቱ አድር ሰው” አለው።