18 ሕፃኑ አደገ፤ አንድ ቀንም አባቱ ከዐጫጆች ጋር ወደነበረበት ቦታ ሄደ።
19 አባቱንም፣ “ራሴን! ራሴን!” አለው። አባቱም አገልጋዩን፣ “ተሸክመህ ወደ እናቱ አድር ሰው” አለው።
20 አገልጋዩም አንሥቶ እናቱ ዘንድ አደረሰው፤ ልጁም እስከ እኩለ ቀን ድረስ በእናቱ ጭን ላይ ተቀመጠ፤ ከዚያም ሞተ።
21 ወደ ላይ ወጥታም በእግዚአብሔር ሰው ዐልጋ ላይ አስተኛችው፤ በሩንም ዘግታበት ወጣች።
22 ከዚያም ባሏን ጠርታ፣ “ወደ እግዚአብሔር ሰው በፍጥነት ደርሼ እንድመለስ አንድ አገልጋይና አንድ አህያ ላክልኝ” አለችው።
23 ባሏም፣ “ዛሬ ወደ እርሱ መሄድ ለምን አስፈለገሽ? መባቻ ወይም ሰንበት አይደል” አላት።እርሷም፣ “ምንም አይደል፤ ልሂድ” አለችው።
24 ከዚያም አህያውን ጭና አገልጋይዋን፣ “ቶሎ ቶሎ ንዳ፤ እኔ ካልነገርኩህ በቀር ለእኔ ብለህ አታዝግም” አለችው።