9 እንዲህም አላቸው፤ “ ‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚሉኝ ለእነዚህ ሰዎች የምትሰጡኝ ምክር ምንድ ነው? ምንስ ብለን እንመልስላቸው?”
10 አብሮ አደጎቹም ወጣቶች እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ለጠየቊህ ሕዝብ፤ ‘አባትህ በላያችን ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ለሚሉህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ይልቅ ትወፍራለች፤
11 አባቴ ከባድ ቀንበር ጫነባችሁ፤ እኔ ግን የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ።”
12 ንጉሡ፣ “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ” ባላቸው መሠረት ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ሮብዓም ተመለሱ።
13 ንጉሡም የሽማግሌዎችን ምክር በመናቅ፣ አመናጭቆ መለሰላቸው፤
14 እርሱም የወጣቶቹን ምክር በመቀበል፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደ፤ እኔ ደግሞ የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው።
15 እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአሒያ አማካይነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ወስኖ ስለ ነበር፣ ንጉሡ ሕዝቡን አላዳመጠም።