2 ዜና መዋዕል 23:1-6 NASV

1 በሰባተኛው ዓመት ዮዳሄ በረታ፤ የመቶ አለቆች ከሆኑት ከይሮሐም ልጅ ከዓዛርያስ፣ ከይሆሐናን ልጅ ከይስማኤል፣ ከዖቤድ ልጅ ከዓዛርያስ፣ ከዓዳያ ልጅ ከማዕሤያ፣ ከዝክሪ ልጅ ከኤሊሳፋጥ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ።

2 እነርሱም ወደ መላው ይሁዳ ሄደው፣ ሌዋውያንንና የእስራኤል ቤት አለቆችን ከየከተማው ሁሉ ሰበሰቡ። ወደ ኢየሩሳሌም በመጡ ጊዜም፣

3 ጉባኤው ሁሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ከንጉሡ ጋር ቃል ኪዳን አደረጉ።ዮዳሄም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ለዳዊት ዘር በሰጠው ተስፋ መሠረት እነሆ፣ የንጉሡ ልጅ ይነግሣል።

4 እንግዲህ እናንተ የምታደርጉት ይህ ነው፤ በሰንበት ዕለት ተረኛ ከሆናችሁት ከእናንተ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ አንድ ሦስተኛው በሮቹን ጠብቁ፤

5 አንድ ሦስተኛው ቤተ መንግሥቱን፣ አንድ ሦስተኛው “የመሠረት ቅጽር በር” የተባለውን ጠብቁ፤ የቀሩት ሰዎች በሙሉ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ ይሁኑ።

6 ተረኛ ከሆኑት ካህናትና ሌዋውያን በቀር ማንም ሰው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አይግባ፤ እነርሱ የተቀደሱ ስለሆኑ ይግቡ፤ የቀሩት ሰዎች በሙሉ ግን፣ ወደ ቤተ መቅደሱ እንዳይገቡ እግዚአብሔር ያዘዘውን ይጠብቁ።