2 ዜና መዋዕል 9:2-8 NASV

2 ሰሎሞንም የጠየቀችውን ሁሉ መለሰላት፤ ሊመልስላት የተሳነው አንዳች ነገር አልነበረም።

3 የሳባ ንግሥት የሰሎሞንን ጥበብና የሠራውን ቤተ መንግሥት፣

4 በገበታው ላይ የሚቀርበውን መብል፣ የሹማምቱን አቀማመጥ፣ አስተናባሪዎቹንና አለባበሳቸውን፣ ጠጅ አሳላፊዎቹንና አለባበሳቸውን እንዲሁም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያቀረባቸውን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ባየች ጊዜ እጅግ ተደነቀች።

5 ንጉሡንም እንዲህ አለችው፤ “ስለ ሥራህና ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ሁሉ እውነት ነው።

6 ነገር ግን መጥቼ በዓይኔ እስካየሁ ጊዜ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም ነበር፤ በርግጥም የጥበብህ እኩሌታ እንኳ አልተነገረኝም፤ እኔ ከሰማሁት ዝና እጅግ ትልቃለህ።

7 ሰዎችህ ምንኛ ታድለዋል! ዘወትር በፊትህ ቆመው ጥበብህን የሚሰሙ ሹማምትህስ ምንኛ ታድለዋል!

8 ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ንጉሥ ሆነህ እንድትገዛ፣ በአንተ ደስ የተሰኘውና በዙፋኑ ላይ ያስቀመጠህ አምላክህ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን፤ አምላክህ ለእስራኤል ካለው ፍቅርና ለዘላለም ሊያጸናቸው ካለው ፍላጎት የተነሣ፣ ፍትሕና ጽድቅ እንዲሰፍን ታደርግ ዘንድ አንተን በላያቸው ላይ አንግሦሃልና።”