6 የብር ሰንሰለት ሳይበጠስ፣የወርቅ ሳሕንም ሳይሰበር፣የውሃ መቅጃው በምንጩ አጠገብ ሳይከሰከስ፣ወይም መንኰራኵሩ በውሃ ጒድጓድ ላይ ሳይሰበር፣
7 ዐፈር ወደ መጣበት መሬት ሳይመለስ፣መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ፣ፈጣሪህን አስብ።
8 ሰባኪው “ከንቱ ከንቱሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” ይላል።
9 ሰባኪው ጥበበኛ ብቻ አልነበረም፤ ነገር ግን ለሕዝቡ ዕውቀትንም ያስተምር ነበር። እርሱም በጥልቅ አሰበ፤ ተመራመረም፤ ብዙ ምሳሌዎችንም በሥርዐት አዘጋጀ።
10 ሰባኪው ትክክለኛውን ቃል ለማግኘት ተመራመረ፤ የጻፈውም ቅንና እውነት ነበረ።
11 የጠቢባን ቃላት እንደ ሹል የከብት መንጃ ናቸው፤ የተሰበሰቡ አባባሎቹም እጅግ ተቀብቅበው እንደ ገቡ ችንካሮች ሲሆኑ፣ ከአንድ እረኛ የተሰጡ ናቸው።
12 ልጄ ሆይ፤ ከዚህ ሁሉ በላይ በማንኛውም ነገር ተጠንቀቅ፤ አንዳችም አትጨምር።ብዙ መጻሕፍትን መጻፍ ማብቂያ የለውም፤ ብዙ ማጥናትም ሰውነትን ያደክማል።