10 ጠላቴም ታያለች፤ኀፍረትንም ትከናነባለች፤“አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?”ያለችኝን፣ዐይኖቼ ውድቀቷን ያያሉ፤አሁንም እንኳ፣እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።
11 ቅጥሮቻችሁን የምትሠሩበት፣ድንበራችሁንም የምታሰፉበት ቀን ይመጣል።
12 በዚያ ቀን ሰዎች፣ከአሦር እስከ ግብፅ ከተሞች፣ከግብፅ እስከ ኤፍራጥስ፣ከባሕር ወደ ባሕር፣ከተራራ ወደ ተራራ ወደ እናንተ ይመጣሉ።
13 ከሥራቸው የተነሣ፣በነዋሪዎቿ ምክንያት ምድር ባድማ ትሆናለች።
14 ብቻቸውን በዱር ውስጥ፣በለመለመ መስክ የሚኖሩትን፣የርስትህ መንጋ የሆኑትን፣ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤እንደ ቀድሞው ዘመን፣በባሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
15 “ከግብፅ እንደ ወጣህበት ዘመን ሁሉ፣ታምራቴን አሳያቸዋለሁ።”
16 አሕዛብ ያያሉ፣ ያፍራሉም፤ኀይላቸውን ሁሉ ያጣሉ፤አፋቸውን በእጃቸው ይይዛሉ፤ጆሮአቸውም ትደነቍራለች።