8 “እነሆ፤ የጌታ እግዚአብሔር ዐይኖች፣በኀጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፤ከምድር ገጽ፣ ፈጽሜ አጠፋዋለሁ፤የያዕቆብን ቤት ግን፣ ሙሉ በሙሉአልደመስስም፤”ይላል እግዚአብሔር።
9 “እነሆ፤ ትእዛዝ እሰጣለሁ፤እህል በወንፊት እንደሚነፋ፣የእስራኤልን ቤት፣በሕዝብ ሁሉ መካከል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።
10 በሕዝቤ መካከል ያሉ፣‘ክፉ ነገር አያገኘንም ወይም አይደርስብንም’ የሚሉ፣ኀጢአተኞች ሁሉ፣በሰይፍ ይሞታሉ።
11 “በዚያ ቀን፣የወደቀውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፤የተሰበረውን እጠግናለሁ፤የፈረሰውን ዐድሳለሁ፤ቀድሞ እንደነበረም አድርጌ እሠራዋለሁ፤
12 ስለዚህ የኤዶምን ትሩፍ፣በስሜ የተጠሩትንም ሕዝቦች ሁሉ ይወርሳሉ፤”ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር።
13 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ ዐጫጁ ዐጭዶ ሳይጨርስ፣ዐራሹ በላዩ የሚደርስበት፣ችግኝ ተካዩም ገና ተክሎ ሳይጨርስ፣ወይን ጨማቂው የሚደርስበት ጊዜ ይመጣል፤አዲስ የወይን ጠጅ ከተራሮች ይንጠባጠባል፤ከኰረብቶችም ሁሉ ይፈሳል።
14 የተሰደደውን ሕዝቤን እስራኤልን እመልሳለሁ፤እነርሱም የፈራረሱትን ከተሞች መልሰው ሠርተው በውስጣቸው ይኖራሉ።የወይን ተክል ተክለው፣ ጠጁን ይጠጣሉ፤አትክልት ተክለው ፍሬውን ይበላሉ።