ዘካርያስ 10:1-7 NASV

1 የበልግ ዝናብ እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ማዕበሉን ደመና የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው፤እርሱ ለሰዎች በቂ ዝናብን፣ለእያንዳንዱም የምድርን ተክል ይሰጣል።

2 ተራፊም አሳሳች ነገር ይናገራል፤ሟርተኞች የሐሰት ራእይ ያያሉ፤የውሸት ሕልም ይናገራሉ፤ከንቱ መጽናናት ይሰጣሉ፤ስለዚህ ሕዝቡ እንደ በጎች ተቅበዘበዙ፤እረኛ በማጣትም ተጨነቁ።

3 “ቍጣዬ በእረኞች ላይ ነዶአል፤መሪዎችንም እቀጣለሁ፤ እግዚአብሔር ጸባኦት፣ለመንጋው ለይሁዳ ቤት ይጠነቀቃልና፤በጦርነትም ጊዜ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።

4 ከይሁዳ፣ የማእዘን ድንጋይ፣የድንኳን ካስማ፣የጦርነት ቀስት፣ገዥም ሁሉ ይወጣል።

5 ጠላትን መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ይረጋግጣሉ፤በአንድነት እንደ ጦር ሰልፈኛ ይሆናሉ፤እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ስለ ሆነ ተዋግተው፤ፈረሰኞችን ያዋርዳሉ።

6 “የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፤የዮሴፍንም ቤት እታደጋለሁ።ስለምራራላቸው፣ወደቦታቸው እመልሳቸዋለሁ፤እነርሱም በእኔ እንዳልተተዉ ሰዎችይሆናሉ፤እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፣ጸሎታቸውን እሰማለሁ።

7 ኤፍሬማውያን እንደ ኀያላን ሰዎች ይሆናሉ፤ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ሐሤት ያደርጋል።ልጆቻቸው ያዩታል፤ ደስተኛም ይሆናሉ፤ልባቸውም በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል።