ዘካርያስ 9:3-9 NASV

3 ጢሮስ ለራሷ ምሽግ ሠርታለች፤ብሩን እንደ ዐፈርወርቁንም እንደ መንገድ ላይ ትቢያ ቈልላለች።

4 ጌታ ግን ሀብቷን ይወስዳል፤በባሕር ያላትንም ኀይል ይደምስሳል፤እርሷም በእሳት ፈጽማ ትጠፋለች።

5 አስቀሎና አይታ ትርዳለች፤ጋዛ በሥቃይ ትቃትታለች፤አቃሮናም እንደዚሁ ትሠቃያለች፤ ተስፋዋ ይመነምናልና።ጋዛ ንጉሥዋን ታጣለች፤አስቀሎናም ባድማ ትሆናለች።

6 ድብልቅ ሕዝቦች አዛጦንን ይይዛሉ፤የፍልስጥኤማውያንንም ትምክሕት እቈርጣለሁ።

7 ደሙን ከአፋቸው፣የተከለከለውንም ምግብ ከመንጋጋቸው አወጣለሁ።የተረፉት ለአምላካችን ይሆናሉ፤በይሁዳም አለቆች ይሆናሉ፤አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።

8 እኔ ግን ቤቴንከዘራፊ ኀይሎች እጠብቃለሁ፤ጨቋኝ ከእንግዲህ ሕዝቤን አይወርስም፤አሁን ነቅቼ እጠብቃለሁና።

9 አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ፣ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖወደ አንቺ ይመጣል።