ዘዳግም 16:14-20 NASV

14 በበዓልህ አንተ፣ ወንድና ሴት ልጅህ፣ ወንድና ሴት አገልጋይህ፣ በከተማው ያለ ሌዋዊ፣ መጻተኛ፣ አባት አልባውና መበለቲቱ ደስ ይበላችሁ።

15 እግዚአብሔር (ያህዌ) በመረጠው ስፍራ ለአምላክህለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በዓሉን ሰባት ቀን አክብር፤ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በእህል ምርትህና በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክሃል፤ ደስታህም ፍጹም ይሆናል።

16 ወንዶችህ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ፣ በቂጣ በዓል፣ በመከር በዓልና በዳስ በዓል ላይ፣ እርሱ በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ይቅረቡ፤ ማንም ሰው በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ባዶ እጁን አይቅረብ።

17 አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በባረከህ መጠን እያንዳንዱ እንደ ችሎታው ይስጥ።

18 አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ።

19 ፍርድ አታዛባ፤ አድልዎ አታድርግ፤ ጒቦም አትቀበል፤ ጒቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።

20 በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ፣ ቅን ፍርድን ብቻ ተከተል።