3 እኔ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም ዐውጃለሁ፤የአምላካችንን (ኤሎሂም) ታላቅነት አወድሱ!
4 እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም (ኤሎሂም) እርሱ ነው።
5 በእርሱ ላይ ክፋት ፈጽመዋል፤ ከነውራቸው የተነሣ ከእንግዲህ ልጆቹ አይደሉም፤ወልጋዳና ጠማማ ትውልዶች ናቸው።
6 አንተ ተላላና ጥበብ የጐደለህ ሕዝብ፣ ለእግዚአብሔር (ለያህዌ) የምትመልስለት በዚህ መንገድ ነውን?አባትህ ፈጣሪህ፣የሠራህና ያበጀህ እርሱ አይደለምን?
7 የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤አባትህን ጠይቅ፤ ይነግርሃልም፤ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ያስረዱሃል።
8 ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ፣የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፣በእስራኤል ልጆች ቊጥር ልክ፣የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ፤
9 የእግዚአብሔር (ያህዌ) ድርሻ የገዛ ሕዝቡ፣ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና።