3 በእርግጥ ሕዝቡን የምትወድ አንተ ነህ፤ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ውስጥ ናቸው።ከእግርህ ሥር ሁሉ ይሰግዳሉ፤ከአንተ ትእዛዝ ይቀበላሉ፤
4 ይህ ሙሴ የሰጠን ሕግ፣የያዕቆብ ጉባኤ ርስት ነው።
5 የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋር ሆነው፣በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፣እርሱ በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር።
6 “ሮቤል በሕይወት ይኑር፤ አይሙት፤የወገኖቹ ቊጥርም አይጒደልበት።”
7 ስለ ይሁዳ የተናገረው ይህ ነው፦“እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ የይሁዳን ጩኸት ስማ፤ወደ ወገኖቹም አምጣው።በገዛ እጆቹ ራሱን ይከላከላል፤አቤቱ ከጠላቶቹ ጋር ሲዋጋ ረዳቱ ሁን!
8 ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦“ቱሚምህና ኡሪምህ፣ለምትወደው ሰው ይሁን፤ማሳህ በተባለው ቦታ ፈተንኸው፤በመሪባም ውሃ ከእርሱ ጋር ተከራከርህ።
9 ስለ አባቱና ስለ እናቱ ሲናገርም፣‘ስለ እነርሱ ግድ የለኝም’ አለ።ወንድሞቹን አልለያቸውም፤ልጆቹንም አላወቃቸውም።ለቃልህ ማን ጥንቃቄ አደረገ፤ኪዳንህንም ጠበቀ።