6 “ሮቤል በሕይወት ይኑር፤ አይሙት፤የወገኖቹ ቊጥርም አይጒደልበት።”
7 ስለ ይሁዳ የተናገረው ይህ ነው፦“እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ የይሁዳን ጩኸት ስማ፤ወደ ወገኖቹም አምጣው።በገዛ እጆቹ ራሱን ይከላከላል፤አቤቱ ከጠላቶቹ ጋር ሲዋጋ ረዳቱ ሁን!
8 ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦“ቱሚምህና ኡሪምህ፣ለምትወደው ሰው ይሁን፤ማሳህ በተባለው ቦታ ፈተንኸው፤በመሪባም ውሃ ከእርሱ ጋር ተከራከርህ።
9 ስለ አባቱና ስለ እናቱ ሲናገርም፣‘ስለ እነርሱ ግድ የለኝም’ አለ።ወንድሞቹን አልለያቸውም፤ልጆቹንም አላወቃቸውም።ለቃልህ ማን ጥንቃቄ አደረገ፤ኪዳንህንም ጠበቀ።
10 ሥርዐትህን ለያዕቆብ፣ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራል።ዕጣን በፊትህ፣የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ በመሠዊያህ ላይ ያቀርባል።
11 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ኀይሉን ሁሉ ባርክለት፤በእጁ ሥራ ደስ ይበልህ፤በእርሱ ላይ የሚነሡበትን ሽንጣቸውን ቊረጠው፤ጠላቶቹንም እንዳያንሠራሩ አድርገህ ምታቸው።”
12 ስለ ብንያም እንዲህ አለ፦“የእግዚአብሔር (ያህዌ) ወዳጅ የሆነ በእርሱ ተጠብቆ በሰላም ይረፍ፤ቀኑን ሙሉ ይጋርደዋልና፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚወደውም ሰው በትከሻዎቹ መካከል ያርፋል።”