ዘዳግም 4:42-48 NASV

42 ይኸውም የቈየ ጠላትነት ሳይኖር፣ በድንገት ባልንጀራውን የገደለ ማናቸውም ሰው ሸሽቶ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመሄድ ሕይወቱን ማትረፍ ይችል ዘንድ ነው።

43 ከተሞቹም በምድረ በዳው በከፍተኛ ቦታ ላይ የምትገኘው ቦሶር ለሮቤላውያን፣ በገለዓድ የምትገኘው ራሞት ለጋዳውያን፣ በባሳን ያለችው ጎላን ለምናሴያውያን ነበሩ።

44 ሙሴ በእስራኤላውያን ፊት የደነገገው ሕግ ይህ ነው።

45 ከግብፅ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው መመሪያዎች፣ ሥርዐቶችና ሕጎች እነዚህ ናቸው፤

46 ይህም ከግብፅ በወጡ ጊዜ በሙሴና በእስራኤላውያን ድል በተደረገው፣ በሐሴቦን በነገሠው፣ በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፣ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በቤተ ፌጎር አጠገብ ባለው ሸለቆ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ነው።

47 ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን፣ የእርሱን ምድርና የባሳንን ንጉሥ የዐግን፣ የሁለቱን አሞራውያን ነገሥታት ምድር ርስት አድርገው ወሰዱ።

48 ይህም ምድር በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ካለው ከአሮዔር አንሥቶ እስከ ሴዎን ተራራ ማለትም እስከ አርሞንዔም የሚደርስ ሲሆን፣