17 እንዲሁም የኤዊያውያን፣ የዑር ኬዋናውያን፣ የሲኒያውያን፣
18 የአራዴዎ ናውያን፣ የሰማሪናውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነበረ።ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤
19 የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ሰቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።
20 እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ናቸው።
21 ለያፌት ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔ ቦር ልጆች ሁሉ ቅደመ አያት ነው።
22 የሴም ልጆች፦ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው።
23 የአራም ልጆች፦ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ ናቸው።