8 እነርሱም፣ “መንጎቹ ሁሉ ተሰብስበው ድንጋዩ ከጒድጓዱ አፍ ካልተንከባለለ በስተቀር አንችልም፤ ከዚያም በጎቹን እናጠጣቸዋለን” አሉ።
9 ያዕቆብ ከእረኞቹ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ፣ ራሔል፣ እረኛ ነበረችና የአባቷን በጎች እየነዳች መጣች።
10 ያዕቆብ የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልን፣ እንዲሁም የአጎቱን የላባን በጎች ሲያይ፣ ወደ ጒድጓዱ ሄዶ ድንጋዩን ከጒድጓዱ አፍ አንከባለለ፤ የአጎቱንም በጎች አጠጣ።
11 ከዚያም ያዕቆብ ራሔልን ሳማት፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ።
12 ያዕቆብም የአባቷ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ለራሔል ነገራት፤ እርሷም ሮጣ ሄዳ ይህንኑ ለአባቷ ነገረችው።
13 ላባም የእኅቱ ልጅ ያዕቆብ መምጣቱን እንደ ሰማ፣ ሊቀበለው ፈጥኖ ወጣ። ዐቅፎ ከሳመውም በኋላ፣ ወደ ቤቱ ይዞት ሄደ። ያዕቆብም ሁኔታውን ሁሉ ለላባ ነገረው።
14 ላባም ያዕቆብን፣ “አንተማ የዐጥንቴ ፍላጭ የሥጋዬ ቊራጭ ነህ” አለው።ያዕቆብ አንድ ወር ሙሉ አብሮት ከተቀመጠ በኋላ፣