ዘፍጥረት 3:16-22 NASV

16 ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤“በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤በሥቃይም ትወልጃለሽ፤ፍላጐትሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤እርሱም የበላይሽ ይሆናል።”

17 አዳምንም እንዲህ አለው፤ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ፣ ‘ከእርሱ አትብላ’ ብዬ ያዘዝሁህን ዛፍ በልተሃልና፣“ከአንተ የተነሣ ምድር የተረገመች ትሁን፤በሕይወትህ ዘመን ሁሉምግብህን ጥረህ ግረህ ከእርሷ ታገኛለህ።

18 ምድርም እሾኽና አሜከላታበቅልብሃለች፤ከቡቃያዋም ትበላለህ።

19 ከምድር ስለ ተገኘህ፣ወደ መጣህበት መሬት እስክትመለስድረስእንጀራህን በፊትህ ላብ ትበላለህ፤ዐፈር ነህናወደ ዐፈር ትመለሳለህ።”

20 አዳምም የሕያዋን ሁሉ እናት ናትና ሚስቱን ሔዋን ብሎ ጠራት።

21 እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ከቈዳ ልብስ አዘጋጅቶ አዳምንና ሚስቱን አለበሳቸው።

22 ከዚያም እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም)፣ “ሰው መልካምንና ክፉውን ለይቶ በማወቅ ረገድ አሁን ከእኛ እንደ አንዱ ሆኗል፤ አሁን ደግሞ እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ቀጥፎ እንዳይበላ፣ ለዘላለምም እንዳይኖር ይከልከል” አለ።