12 ዮሴፍም ልጆቹን ከእስራኤል ጒልበት ፈቀቅ በማድረግ አጐንብሶ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ።
13 ከዚያም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ኤፍሬምን ከራሱ በስተ ቀኝ፣ ከእስራኤል በስተ ግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተ ግራ፣ ከእስራኤል በስተ ቀኝ በኩል አቀረባቸው።
14 እስራኤል ግን ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረ፤ ግራ እጁንም በቀኝ እጁ ላይ አስተላልፎ በበኵሩ በምናሴ ራስ ላይ አኖረ።
15 ከዚህ በኋላ ዮሴፍን ባረከ፤ እንዲህም አለው፤“አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱየተመላለሱት እግዚአብሔር (ኤሎሂም)፣ለእኔም እስከ ዛሬ ድረስበዘመኔ ሁሉ እረኛ የሆነኝ አምላክ (ኤሎሂም)፣
16 ከጒዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤እነርሱም በስሜ፣በአባቶቼ በአብርሃምናበይስሐቅ ስም ይጠሩ፤በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።
17 ዮሴፍ፣ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማድረጉን ሲያይ ተከፋ፤ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንሥቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤
18 ዮሴፍም፣ “አባቴ ሆይ፤ እንዲህ አይደለም በኵሩ ይህኛው ስለ ሆነ፣ ቀኝ እጅህን እርሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው።