ዘፍጥረት 49:25-31 NASV

25 አንተን በሚረዳህ በአባትህ አምላክ፣በሚባርክህ፣ ሁሉን ማድረግ በሚችል አምላክ፣ከላይ ከሰማይ በሚገኝ ረድኤት፣ከምድር ጥልቅ በሚገኝ በረከት፣ከማሕፀንና ከጡት በሚገኝ ምርቃት ይባርክሃል።

26 ከጥንት ተራሮች በረከት፣ከዘላለም ኰረብቶች ምርቃት ይልቅ፣የአባትህ በረከት ይበልጣል፤ይኸ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ፤በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ግንባር ላይ ይረፍ።

27 ብንያም፣ ነጣቂ ተኵላ ነው፤ያደነውን ማለዳ ይበላል፤የማረከውን ማታ ይከፋፈላል።

28 እነዚህ ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው። ይህም እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው በረከት አባታቸው ሲባርካቸው የተናገረው ቃል ነው።

29 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “እነሆ፤ ወደ ወገኖቼ የምሰበሰብበት ጊዜ ደርሶአል፤ በኬጢያዊው በኤፍሮን ዕርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ዘንድ ቅበሩኝ፤

30 ይህ በከነዓን ምድር፣ በመምሬ አጠገብ፣ በማክፌላ ዕርሻ ውስጥ ያለው ዋሻ፣ የመቃብር ቦታ እንዲሆን አብርሃም ከኬጢያዊው ኤፍሮን ላይ ከነዕርሻ ቦታው የገዛው ነው።

31 በዚያ አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ተቀብረዋል፤ በዚያ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ተቀብረዋል፤