10 ከዚህ በኋላ ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤“አሁን የአምላካችን ማዳን፣ ኀይልናመንግሥት፣የእርሱ ክርስቶስ ሥልጣንም መጥቶአል።ቀንና ሌሊት በአምላካችን ፊት ሲከሳቸውየነበረው፣የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።
11 እነርሱም በበጉ ደም፣በምስክርነታቸውም ቃል፣ድል ነሡት፤እስከ ሞት ድረስ እንኳ፣ለነፍሳቸው አልሳሱም።
12 ስለዚህ ሰማያት ሆይ፣በውስጣቸውም የምትኖሩ ሆይ፣ደስ ይበላችሁ፤ምድርና ባሕር ግን ወዮላችሁ ምክንያቱም ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን ብቻእንደ ቀረው ስላወቀ፣በታላቅ ቍጣ ተሞልቶ ወደ እናንተ ወርዶአል።
13 ዘንዶው ወደ ምድር እንደተጣለ ባየ ጊዜ፣ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።
14 ሴቲቱም በበረሓ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ መሄድ እንድትችል ሁለት የታላቁ ንስር ክንፎች ተሰጣት፤ ይህም የሆነው በዚያ ከእባቡ ፊት ርቃ ለአንድ ዘመን፣ ለዘመናትና ለዘመን እኩሌታ በክብካቤ እንድትኖር ነው።
15 እባቡም ሴቲቱ በጐርፍ ተጠራርጋ እንድትወሰድ፣ እንደ ወንዝ ያለ ውሃ ከአፉ ተፋ።
16 ምድር ግን ሴቲቱን ረዳቻት፤ አፏንም ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠች።