21 ዐሥራ ሁለቱም በሮች ዐሥራ ሁለት ዕንቈች ነበሩ፤ እያንዳንዱም በር ከአንድ ዕንቍ የተሠራ ነበረ። የከተማዪቱም አውራ መንገድ እንደ መስተዋት ብርሃን የሚያስተላልፍ ንጹሕ ወርቅ ነበረ።
22 ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክና በጉ መቅደሷ ስለሆኑ፣ በከተማዪቱ ውስጥ ቤተ መቅደስ አላየሁም።
23 የእግዚአብሔር ክብር ብርሃን ስለሚሰጣትና በጉም መብራቷ ስለ ሆነ፣ ከተማዋ ፀሓይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጋትም።
24 ሕዝቦች በብርሃኗ ይመላለሳሉ፤ የምድር ነገሥታትም ክብራቸውን ወደ እርሷ ያመጣሉ።
25 በዚያ ሌሊት ስለሌለ፣ በሮቿ በየትኛውም ቀን አይዘጉም።
26 የሕዝቦች ግርማና ክብር ወደ እርሷ ይገባሉ።
27 በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በስተቀር፣ ርኵሰትን የሚያደርግና ውሸትን የሚናገር ሁሉ አይገባባትም።