3 እንግዲህ አንተ ሰው በሌሎች ላይ እየፈረድህ፣ ያንኑ የምታደርግ ከሆነ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃል?
4 ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሓ የሚመራህ መሆኑን ሳትገነዘብ፣ የቸርነቱን፣ የቻይነቱን የትዕግሥቱን ባለጠግነት ትንቃለህ?
5 ነገር ግን በድንዳኔህና ንስሓ በማይገባ ልብህ ምክንያት ትክክለኛ ፍርዱ ሲገለጥ በእግዚአብሔር የቊጣ ቀን በራስህ ላይ ቊጣን ታከማቻለህ።
6 እግዚአብሔር “ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይሰጠዋል”፤
7 በጎ የሆነውን ጸንቶ በማድረግ ክብርን፣ ሞገስንና ዘላለማዊነትን ለሚሹ የዘላለም ሕይወት ይሰጣቸዋል።
8 ነገር ግን በራስ ወዳዶች፣ እውነትን ትተው ክፋትን በሚከተሉ ፍርድና ቊጣ ይደርስባቸዋል።
9 ክፉ በሚያደርግ በማንኛውም ሰው፣ አስቀድሞ በአይሁድ ከዚያም በአሕዛብ ላይ መከራና ጭንቀት ይሆናል፤