12 ሁሉም ተሳስተዋል፤በአንድነት የማይጠቅሙ ሆነዋል፤በጎ የሚያደርግ ማንም የለም፤አንድም እንኳ።”
13 “ጒሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤አንደበታቸው ሽንገላን ያዘወትራል።”“በከንፈሮቻቸው የእባብ መርዝ አለ።”
14 “አፋቸው ርግማንና ምሬት ሞልቶበታል።”
15 “እግራቸው ደም ለማፍሰስ ፈጣን ነው፤
16 በመንገዳቸው ጥፋትና ጒስቊልና ይገኛል፤
17 የሰላምንም መንገድ አያውቁም።”
18 “በዐይናቸው ፊት የእግዚአብሔር ፍርሀት የለም።”