7 ጣዖቶችዋ ሁሉ ይሰባበራሉ፤ለቤተ መቅደሷ የቀረበው ገጸ በረከት በእሳት ይቃጠላል፤ምስሎችዋን ሁሉ እደመስሳለሁ፤ገጸ በረከቷን በዝሙት አዳሪነት እንደ ሰበሰበች ሁሉ፣አሁንም ገጸ በረከትዋ የዝሙት አዳሪነት ዋጋ መቀበያ ይሆናል።
8 በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፤እንደ ጒጒትም አቃስታለሁ።
9 ቊስሏ የማይሽር ነውና፤ለይሁዳ ተርፎአል፤እስከ ሕዝቤ መግቢያ በር፣እስከ ኢየሩሳሌም እንኳ ደርሶአል።
10 በጌት አታውሩት፤ከቶም አታልቅሱ፤በቤትዓፍራ፣በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።
11 እናንት በሻፊር የምትኖሩ፣ዕርቃናችሁን ሆናችሁ በኀፍረት ዕለፉ፤በጸዓናን የሚኖሩከዚያ አይወጡም፤ቤትዔጼል በሐዘን ላይ ናት፤ለእናንተም መጠጊያ ልትሆን አትችልም።
12 ከመከራው መገላገልን በመሻት፣በማሮት የሚኖሩ በሥቃይይወራጫሉ፤እስከ ኢየሩሳሌም በር ሳይቀር፣ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአልና።
13 እናንት በለኪሶ የምትኖሩ፣ፈረሶችን ከሠረገላው ጋር አያይዙ፤ለጽዮን ሴት ልጅ፣የኀጢአት መጀመሪያ እናንት ነበራችሁ፤የእስራኤል በደልበእናንተ ዘንድ ተገኝቶአልና።