21 ክፉ ሳይቀጣ እንደማይቀር ዕወቅ፣ጻድቃን ግን በነጻ ይሄዳሉ።
22 በእርያ አፍንጫ ላይ እንደ ተሰካ የወርቅ ቀለበት፣ማስተዋል የጐደላት ቆንጆ ሴት እንዲሁ ናት።
23 የጻድቃን ምኞት ምንጊዜም ፍጻሜው ያማረ ነው፤የክፉዎች ተስፋ ግን በቊጣ ያከትማል።
24 አንዱ በለጋስነት ይሰጣል፤ ሆኖም ይበልጥ ያገኛል፤ሌላው ያለ መጠን ይሰስታል፤ ግን ይደኸያል።
25 ለጋስ ይበለጽጋል፤ሌሎችን የሚያረካም ራሱ ይረካል።
26 በድብቅ እህል የሚያከማቸውን ሕዝብ ይረግመዋል፤አውጥቶ የሚሸጥ ግን በረከት ይጐናጸፋል።
27 በጎ ነገርን ተግቶ የሚሻ በጎ ነገር ይጠብቀዋል፤ክፉ ነገር የሚፈልገውን ግን ክፉ ያገኘዋል።