1 ተግሣጽን የሚወድ ዕውቀትን ይወዳል፤መታረምን የሚጠላ ግን ደነዝ ነው።
2 መልካም ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ያገኛል፤ተንኰለኛውን ግን እግዚአብሔር ይፈርድበታል።
3 ሰው በክፋት ላይ ተመሥርቶ ሊጸና አይችልም፤ጻድቃን ግን ከቦታቸው አይነቃነቁም።
4 መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት፤አሳፋሪ ሚስት ግን ዐጥንቱ ውስጥ እንዳለ ንቅዘት ናት።
5 የጻድቃን ሐሳብ ቀና ነው፤የክፉዎች ምክር ግን ሸር አለበት።
6 የክፉዎች ቃል ደም ለማፍሰስ ታደባለች፤የቅኖች ንግግር ግን ይታደጋቸዋል።