13 ምክርን የሚያቃልል በራሱ ላይ ጥፋት ያመጣል፤ትእዛዝን የሚያከብር ግን ወሮታን ይቀበላል።
14 የጠቢብ ትምህርት የሕይወት ምንጭ ናት፤ሰውን በሞት ወጥመድ እንዳይያዝ ታደርገዋለች።
15 መልካም ማስተዋል ሞገስን ታስገኛለች፤የከዳተኞች መንገድ ግን አስቸጋሪ ነው።
16 አስተዋይ ሰው ሥራውን በዕውቀት ያከናውናል፤ተላላ ግን ሞኝነቱን ይገልጣል።
17 ክፉ መልእክተኛ መከራ ውስጥ ይገባል፤ታማኝ መልእክተኛ ግን ፈውስን ያመጣል።
18 ተግሣጽን የሚንቅ ወደ ድኽነትና ኀፍረት ይሄዳል፤ዕርምትን የሚቀበል ሁሉ ግን ይከበራል።
19 ምኞት ስትፈጸም ነፍስን ደስ ታሰኛለች፤ተላሎች ግን ከክፋት መራቅን ይጸየፋሉ።