1 ጠቢብ ሴት ቤቷን ትሠራለች፤ተላላ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች።
2 አካሄዱ ቅን የሆነ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፤መንገዱ ጠማማ የሆነ ግን ይንቀዋል።
3 የተላላ ሰው ንግግር ለጀርባው በትር ታስከትልበታለች፤የጥበበኛ ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።
4 በሬዎች በሌሉበት ገንዳው ባዶ ይሆናል፤በበሬ ጒልበት ግን ብዙ ምርት ይገኛል።
5 ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይዘከዝካል።
6 ፌዘኛ ጥበብን ይሻል፤ ሆኖም አያገኛትም፤ዕውቀት ግን ለአስተዋዮች በቀላሉ ትገኛለች።
7 ከተላላ ሰው ራቅ፤ከከንፈሮቹ ዕውቀት አታገኝምና።