28 የሕዝብ ብዛት የንጉሥ ክብር ሲሆን፣የዜጐች ማነስ ግን ለገዥ መጥፊያው ነው።
29 ታጋሽ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ግልፍተኛ ሰው ግን ቂልነትን ይገልጣል።
30 ሰላም ያለው ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል፤ቅናት ግን ዐጥንትን ያነቅዛል።
31 ድኾችን የሚያስጨንቅ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤ለተቸገሩ የሚራራ ሁሉ ግን አምላክን ያከብራል።
32 ክፉዎች በክፋታቸው ይወድቃሉ፤ጻድቃን ግን በሞት ጊዜ እንኳ መጠጊያ አላቸው።
33 ጥበብ በአስተዋዮች ልብ ታድራለች፤በተላሎች መካከል ራሷን ትገልጣለች።
34 ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ኀጢአት ግን ለየትኛውም ሕዝብ ውርደት ነው።