14 ክፉ በመሥራት ደስ የሚላቸው፣በክፋት ጐዳና ሐሤት የሚያደርጉ፣
15 መንገዳቸው ጠማማ፣በአካሄዳቸው ጠመዝማዞች ናቸው።
16 ከአመንዝራ ሴትም ትጠብቅሃለች፤በአንደበቷም ከምታታልል ዘልዛላ ታድንሃለች፤
17 ይህችም የልጅነት ባሏን የተወች፣በአምላኳ ፊት የገባችውን ኪዳን ያቃለለች ናት።
18 ቤቷ ወደ ሞት ያደርሳል፤መንገዷም ወደ መናፍስተ ሙታን ያመራል።
19 ወደ እርሷ የሚገባ ማንም አይመለስም፤የሕይወትንም መንገድ አያገኝም።
20 አንተም በደጋግ ሰዎች ጐዳና ትሄዳለህ፤የጻድቃንንም መንገድ ይዘህ ትጓዛለህ።