23 አንደበቱንና ምላሱን የሚቈጣጠር፣ራሱን ከመቅሠፍት ይጠብቃል።
24 ትዕቢተኛና ኵሩ ሰው፣ ኋፌዘኛቃ ይባላል፤በጠባዩም እብሪተኛ ነው።
25 ታካችን የሚገድለው ምኞቱ ነው፤እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።
26 ክፉ ሰው ቀኑን ሙሉ ይመኛል፤ጻድቅ ግን አንዳች ሳያስቀር ይሰጣል።
27 የክፉ ሰው መሥዋዕት አጸያፊ ነው፤በክፉ ዐላማ ሲያቀርብማ የቱን ያህል አስከፊ ይሆን!
28 ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤እውነቱን የሚናገር ግን ጸንቶ ይኖራል።
29 ክፉ ሰው በዐጒል ድፍረት ይቀርባል፤ቅን ሰው ግን አደራረጉን ያስተውላል።