11 ታዳጊያቸው ብርቱ ነውና፤እርሱ ይፋረድላቸዋል።
12 ልብህን ለምክር፣ጆሮህንም ለዕውቀት ቃል ስጥ።
13 ልጅን ከመቅጣት ወደ ኋላ አትበል፤በአርጩሜ ብትገርፈው አይሞትም።
14 በአርጩሜ ቅጣው፤ነፍሱንም ከሞት አድናት።
15 ልጄ ሆይ፤ ልብህ ጠቢብ ቢሆን፣የእኔም ልብ ሐሤት ያደርጋል፤
16 ከንፈሮችህ ትክክሉን ቢናገሩ፣ውስጣዊ ሁለንተናዬ ሐሤት ያደርጋል።
17 ልብህ በኀጢአተኞች አይቅና፤ነገር ግን ዘወትር እግዚአብሔርን ለመፍራት ትጋ።